ሰላም! አገልግሎቶቼ ለክርስቶስ አካል ብቻ ናቸው።
መረጃዬን ከማያምኑ ጋር እንዳትካፈሉ እለምናለሁ። አመሰግንሃለሁ።

በሰርትፊኬት እውቅና ያገኜ፡
የብሪት-ሚላ አገልግሎት ሰጭ፡
ለመሲያኒክ አማኞች
መልካም እንክብካቤ በመስጠት እና ሁሉንም ቀለል ባለ አቀራረብ በማድረግ በታማኝነት አገለግላለሁ።
ይህ ድህረ ገጽ በመገንባት ላይ ነው። ተከታተሉት!
ሻሎም፡ ሥሜ ሞሼ ሲሆን በእየሱስ የማምን አይሁዳዊ ነኝ።
ለ 20 ዓመት በላይ የሚሆን፡ የመስያኒክ አይሁድ አማኞችን ለማገልገል እድሉን አግኝቻለሁ።
ይኸንም ሳደርግ የአይሁድን የእምነት ስርአቶች እና የመጸሐፍ ቅዱስን የህይወት መርሖች በአክብሮት በመከተል ነው። የቀደሙት የእምነት ስርዕቶች በውስጣቸው ጥልቅ የሆኑ ቅድስናና ውበት የያዙ በመሆናቸው እንዲህ እያገለገልኩ ቅይቻለሁ።
እግዚያብሔር የቀደሰውና በመንፍሱም ያበረታው ህዝብ እንደመሆናችን በቅድስና እንድንኖር እና ደቀመዝሙር እንድናደርግ ተጠርተናል።
በእስራኤል ያለዉን መስያኒክ አይሁድ እንዳገለግል ዕድሉን በማግኜቴ ትልቅ ደስታዬ ይሰማኛል።
በተለይ፡ ወላጆች የተወደደውን ወንድ ልጃቸውን ሲታቅፉ ማየት፤ ከዚያም ከአብርሀም የቃልኪዳን - ኪዳን ጋር የሚያስተሳስራቸዉን የብሪት ሚላ ስርዓት እንዲፍፅሙ መርዳትም ትልቁም ተልዕኮዬ ጭምር ስለሆነ ነው።
ምን አልባት ብዙ ጥያቄ ሊኖሯቹህ ይችላል፡- ልጄ የግርዛት ስርዓት ሲደረግለት ምን ይሆን? ለዚህ ልዩ የሆነ ቀን እንዴት እንዘጋጅ?
ከሁሉ በላይ ደግሞ፡ ብሪት -ሚላ ለልጃችን ፍቅርና እንክብካቤ በተሞላበት የሚገርዝልን ሰው እንዴት እንምረጥ?
ሥለዚህ ለእነኝህ ጥያቄወች መልስ፡ እባክዎትን ከታች የተጻፍውን ያንብቡ፡ ደግሞም ወደ ሁዋላ ሳይሉ ለማንኛውም ጥያቄዎ በመደወል ልረዳዎ ዝግጁ እንደሆንኩ ላሳስበዎ እውዳለሁ። በዕብራይስጥ እና በእንግሊዝኛ መናገር እችላለሁ።
እናንተን ማገልገል ደስታዬ ነው።